Search

በሩብ ዓመት ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 48 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

ማክሰኞ ጥቅምት 04, 2018 58

በ2018 በጀት ሩብ ዓመት ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 48 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) አስታውቀዋል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻፀም ሪፖርት የግምገማ መድረክ ተካሂዷል።
 
በወቅቱ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፤ በወጪ ንግዱ ለተገኘው ውጤት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዋል።
በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ምርቶችን መላክ መጀመሩ ትልቅ ስኬት መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ፤ በተጨማሪም ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል እንድትሆን እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።
በቅድስት ማሞ