Search

ለኢኮኖሚ ዕድገቱ አስፈላጊ የሆነው የሠለጠነ የሠው ኃይል

ማክሰኞ ጥቅምት 04, 2018 44

ኢትዮጵያ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን እየተገበረች ይገኛል፡፡ በሌላ በኩልም በርካቶች ወደቢዝነስ ዓለሙ በስፋት እየተቀላቀሉ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ይበልጥ እያደገ እንዲጓዝ የሠው ኃይል ልማት ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ደግሞ ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር ቆይታ ያደረጉት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዘመዴነህ ንጋቱ ናቸው።
ገበያ መር የሆነ ኢኮኖሚ ለመገንባት በሚደረግ እንቅስቃሴ ውስጥ ስለኢኮኖሚው ተገቢው ዕውቀት ያለው የሠው ኃይል ማፍራት ላይ ትኩረት መደረግ እንደአለበትም አንስተዋል።
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ የኤክስፖርት ገቢ እየተገኘ መሆኑን የጠቆሙት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው፤ ይህንን ለማጠናከርም በዘርፉ ይበልጥ መሥራት የሚችል ብቁ የሠው ኃይል በስፋት ያስፈልጋል ይላሉ።
የኢትዮጵያ ትልቁ ሀብቷ ወጣቱ ኃይል በመሆኑ ትምህርት ላይ ይበልጥ ኢንቨስት ሊደረግ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያ አቅሟን ለማሳደግ እየወሰደችው ያለው ገበያ መር የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውጤቶች እየታዩበት ቢሆንም፤ አሁንም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በርካታ ሥራዎች እንደሚጠበቁም አመላክተዋል።
 
በሜሮን ንብረት