ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀድሞው የኬኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኤክስ ገጻቸው ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ፤ በቀድሞ የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ህልፈት በኢትዮጵያ መንግስት ስም የተሰማኝን ሀዘን እገልጻለሁ ብለዋል።
የቀድሞው የኬኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ባደረባቸው የልብ ሕመም ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በ80 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተዘግቧል፡፡