የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ከዓለም ባንክ እና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዓመታዊ ጉባዔ ጎን ለጎን በ114ኛው ኢንተርገቨርንመንታል የቡድን 24 ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል።
በወቅቱም ሚኒስትሩ አዳጊ ሀገራት ትክክለኛ ድምፅ እና በቂ ሃብት እንዲያገኙ ብዝኀነት ያለው ዓለም አቀፍ ፍትሐዊ ሥርዓት ሊኖር ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ለአዳጊ ሀገራት ኢኮኖሚ ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ እንዲሁም ለረጅም ጊዜ ልማት የሚያገለግል ፍትሐዊ የፋይናንስ አቅርቦት አስፈላጊነት መሆኑንም አጽንዖት ሰጥተዋል።
በተለይም የተጠናከረ የገንዘብ ድጋፍ እና ትብብር ወሳኝ መሆናቸውን አመላክተዋል።
በጌትነት ተስፋማርያም
 
                                                 
                                                                 
                                                                 
                                                                 
                                                                 
                                            