Search

ፋብሪካዎቹ ወደ ምርት እንዲገቡ መንግሥት ድጋፍ ያደርጋል :- የአማራ ክልል

ዓርብ ጥቅምት 07, 2018 87

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በአንጎለላና ጠራ ወረዳ እና በቡልጋ ከተማ እየተገነቡ የሚገኙ ፋብሪካዎችን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) ፣ ከተለያዩ የቢሮ ኃላፊዎች እና የዞን የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተመልክተዋል።
በአንጎለላና ጠራ ወረዳ ጨኪ ከተማ ላይ እየተገነባ ያለው የጀር የተቀናጀ የምግብ ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ በቡልጋ ከተማ አስተዳደር በመገንባት ላይ የሚገኙትን የሴራሚክና የወረቀት ፋብሪካዎች ናቸው የተጎበኙት።
በዚሁ ጊዜ በመንግሥትና በባለሃብቶች መካከል ያለው ጠንካራ ግንኙነት የተሻለ መሆኑ እና የፋብሪካ ግንባታ ሂደቱ በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።
የሚገነቡት ፋብሪካዎች ተጠናቅቀው ወደ ምርት ሲገቡ ተኪ ምርት በማምረት ፣ የውጭ ምንዛሪ በማዳን ፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ በኩል ፋይዳቸው ከፍተኛ እንደሆነ ተነስቷል።
ፋብሪካዎቹ በተያዘላቸው ጊዜ ወደ ምርት እንዲገቡም በመንግሥት በኩል አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ እንደሚደረግ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል።