በኦሮሚያ ክልል የአረንጓዴ አሻራ የእንክብካቤ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ በተገኙበት ተጀምሯል፡፡
በክልሉ ባለፈው የክረምት ወቅት 4.9 ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ያነሱት ኃላፊው፤ በክልሉ በሁሉም ዞኖች እና ወረዳዎች የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ሥራ መጀመሩን አንስተዋል፡፡
አሲዳማ የሆኑ አካባቢዎችን በአረንጓዴ አሻራ የመሸፈን ስራ የተከናወነ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው፤ ከተተከሉት ችግኞች 87 በመቶ የሚሆኑት የጸደቁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በክልሉ የደን ሽፋን በአጠቃላይ ከ27 በመቶ በላይ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህም በተከታታይ ዓመታት የተሰራው የአረንጓዴ አሻራ ውጤት መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዓሊ ደደፎ
#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #Oromia #GreenLegacy