የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በክልሉ በመገንባት ላይ ያሉ፣ የተጠናቀቁ እና አዳዲስ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
የርዕሰ መስተዳድሩ የመስክ ምልከታ የገጠር ኮሪደሮችን፣ የቅርስ ጥበቃ ሥራዎችን፣ የመንገድ ፕሮጀክቶችን፣ የመንገድ ዳር መብራቶችን፣ ሼዶችን፣ የሌማት ትሩፋት እንቅስቃሴዎችን እና የመናኸሪያ አገልግሎት መስጫ ስፍራ ግንባታዎችን ያካተተ ነው።
በወቅቱ አቶ ኦርዲን በድሪ፤ የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ማሳደግ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል።

የተጀመሩ የልማት ሥራዎች በፍጥነት መጠናቀቅ አለባቸው ያሉት አቶ ኦርዲን በድሪ፤ ፕሮጀክቶችን በተቻለ ፍጥነት ወደ ሥራ በማስገባት የኅብረተሰቡ ተጠቃሚነት ማሳደግ ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።
በቴዎድሮስ ታደሰ