በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን፣ በቡኖ በደሌ፣ በወለጋ እና ኢሉባቦር አካባቢዎች የሻይ ቅጠል ምርት በስፋት እየተመረተ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል።
ቀደም ሲል በባህር ዛፍ ተሸፍነው የቆዩ የተመረጡ ስፍራዎች አሁን ላይ በሻይ ቅጠል ምርት መተካታቸውም ተጠቁሟል።
በክረምት ወቅት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በተተከሉ ችግኞች በ1500 ሔክታር መሬት ላይ የሻይ ቅጠል ልማት እየተከናወነ መሆኑን ያስታወቁት የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ጌቱ ገመቹ ናቸው።
ኃላፊው አክለውም፤ በቀጣይም የሻይ ቅጠል ችግኝ በስፋት በተተከለባቸው አካባቢዎች የሻይ ቅጠል ማቀነባበሪያ ማሽኖችን በመትከል አርሶ አደሮች በቀላሉ ምርታቸውን ለሀገር ውስጥ እንደዚሁም ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።
በራሄል አብደላ