የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን ሥርዓተ ቀብር ለማስፈፀም የተቋቋመው ኮሚቴ በሰጠው መግለጫ መሠረት፥ ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ 10 ሰዓት ላይ በኑዛዜያቸው መሠረት ኃይሌ ጋርመንት ሰፈራ ከአዲሱ አትክልት ተራ ትንሽ ዝቅ ብሎ ቁርዓን ያስተምሩበት በነበረው መስጂድ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይፈፀማል።
ሶላተል ጀናዛ ለበርካታ ዓመታት ባስተማሩበት እና ፒያሳ በሚገኘው ኑር (በኒ) መስጂድ ዝሁር (ከቀኑ 6 ሰዓት) ላይ ይከናወናል።
ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ደግሞ በአዲስ አበባ ሚሌኒየም አዳራሽ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የአስከሬን ሽኝት ፕሮግራም ይከናወናል።
በላሉ ኢታላ