አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት በተለያዩ የሕክምና ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 263 አዳዲስ ባለሙያዎችን በድምቀት አስመርቋል።
የዘንድሮውን ምረቃ ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ከሕክምና ትምህርት ቤት 3.95 CGPA በማምጣት የከፍተኛ ውጤት ባለቤትና የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ ለመሆን የበቃችው ዶ/ር ሜሮን ለገሰ ስኬት ነው።
ዶ/ር ሜሮን በምረቃው ወቅት ባስተላለፈችው መልዕክት፤ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሴት ተማሪዎች ውጤታማነትና ተሳትፎ እየተሻሻለ መምጣቱን ጠቅሳለች።
በቆይታዋ ያገኘችውን ዕውቀት ለሀገሯና ለወገኖቿ በቅንነት ለማገልገል ዝግጁ መሆኗንም ስለመግለጿ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።