Search

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ የብዙዎች አባት፣ የሰላም እና የአንድነት ተምሳሌት ነበሩ - የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን

ሰኞ ጥቅምት 10, 2018 75

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ኅልፈተ ሕይወት የተሰማትን ኀዘን ገልጻለች።

የቤተክርስቲያኗ የጳጳሳት ጉባዔ ባስተላለፈው የኀዘን መግለጫ፥ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ የብዙዎች አባት፣ የሰላም እና የአንድነት ተምሳሌት እንደነበሩ ገልጿል። 

ኢትዮጵያ ታላቅ አባት አጥታለች ያለው የጳጳሳት ጉባኤው፥ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ከኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋር በተለይ በሀገሪቱ ሰላም እና እርቅን ለማውረድ በርካታ ሥራዎችን በጋራ መሥራታቸውን አንስቷል። 

የጳጳሳት ጉባኤው ቤተክርስቲያኗ በእኚህ ታላቅ አባት ኅልፈተ ሕይወት የተስማትን ኀዘን ገልጾ፤ ለቤተቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለእስልምና እምነት ተከታዮች እና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እውነተኛ መጽናናትን ተመኝቷል።