የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ኅልፈተ ሕይወት የተሰማውን ኀዘን ገልጿል።
ካውንስሉ በኀዘን መግለጫው፥ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ ተወዳጅ፣ ፍቅር እና መቻቻልን በማስተማር የሚታወቁ፣ የሙስሊሙ ህብረተሰብ መሪ እና አባት እንደነበሩ ገልጿል።
ካውንስሉ ለመላው ሙስሊም ህብረተሰብ እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝቷል።