Search

ባሌ ለኢትዮጵያ የሚተርፍ ሃብትን የያዘ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሰኞ ጥቅምት 10, 2018 46

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀድሞ እና በሥራ ላይ ካሉ አመራሮች ጋር በአደረጉት ውይይት፤ ባሌ ሰፊ ሃብት ያለበት እና ብናርሰው እና ብናለማበት ቶሎ የሚያልቅ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።
ባሌ ለሁላችንም ይበቃል፤ ካለንበት ሁኔታ ወጥተን እንዴት ነው ሃገር ልናሳድግ የሚገባው የሚለውን ሌሎች ማነቃቃት እና ይበልጥ እንዲሰሩ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
በትውልዱ ውስጥ የተሻለ መነቃቃትን የሚፈጥር ነገር መፍጠርም ያስፈልጋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስረድተዋል።
 
በላሉ ኢታላ