Search

ሰላማችንን ጠብቀን ከሄድን በጣም ብሩህ የሆነ የወደፊት ዕድል እንዳለን ይታየኛል - ሌተናል ጄኔራል ፃድቃን ገ/ትንሣኤ

ሰኞ ጥቅምት 10, 2018 37

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀድሞ እና በሥራ ላይ ካሉ አመራሮች ጋር በአደረጉት ‘የሶፍ ኡመር ወግ’ ውይይት ላይ የተካፈሉት ሌተናል ጄኔራል ፃድቃን ገ/ትንሣኤ ብሩህ ነገር ይታየኛል ብለዋል።
በባሌ ዞን ያየሁት ፍፁም ከገመትኩት በላይ ነው ያሉት ሌተናል ጄኔራል ፃድቃን ፤ አካባቢው በዚህ ልክ ሰፊ የሆነ የመሬት እና የውኃ ሃብት እንዲሁም የኢኮሎጂ ሃብት እንዳለው አላውቅም ነበር ሲሉ ተናግረዋል።
ባሌ ላይ ያሉ ወንዞችን በመጠቀም በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ሄክታር ነው እየለማ የሚገኘው፤ ይህንን ስታይ የሚያጭረው ተስፋ ትልቅ ነው ብለዋል።
ሶፍኡመር ዋሻ በሚመች መንገድ እየተዘጋጀ ነው፤ ከመሬት በላይ ያለው ነው የለማው ከመሬት በታች ያለው ሃብት ደግሞ ይለማል ሲሉም ገልፀዋል።
ሰላማችንን ጠብቀን እየተቻቻልን የፖለቲካ ስርዓታችንን ችግር በሚፈታ መልክ አስተካክለን ከሄድን በጣም ብሩህ የሆነ የወደፊት ዕድል እንዳለን ይታየኛል ብለዋል።
ችግሮቻችንን በሰላም በመፍታት ለሀገር የሚጠቅም ነገር ከአደረግን እንዲሁም ኢኮኖሚውም ሲሻሻል የፖለቲካ ስርዓታችም እንደሚስተካከል ተስፋ ይሰጣል ሲሉ ሌተናል ጄኔራል ፃድቃን ተናግረዋል።
 
በጌትነት ተስፋማርያም