Search

የቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክቶች አሁን ለኢትዮጵያ ብርቅ አይደሉም - አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ

ማክሰኞ ጥቅምት 11, 2018 47

በራስ አቅም የሚገነቡ የቢሊዮን ዶላር ሜጋ ፕሮጀክቶች አሁን ለኢትዮጵያ አዲስ አይደሉም ሲሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ እና አማካሪው አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ገለፁ፡፡

ከኢቢሲዶትስትሪም ጋር ቆይታ ያደረጉት አቶ ዘመዴነህ፤ ጀምሮ የመጨረስ አቅም ያላበሰን የእንችላለን ስሜት ዛሬ ላይ ግዙፍ የሆኑ ፕሮጀክቶችን እንድንጀምር አድርጎናል ሲሉ ተናግረዋል፡:

በተለይም ከለውጡ በኋላ የተሰሩ የልማት ስራዎች የሚያስደንቁ ከመሆናቸው የተነሳ “በውስጥ አቅም ብቻ የተከወኑ አይደሉም" በማለት የሚሞግቱ አሉ፤ ይህም የሥራችን ግዝፈት ማሳያ ነው” ብለዋል::

ትልቁ የአውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት እንዲሁም 7ቱ የ30 ቢሊዮን ዶላር የጉባ ብስራቶች ደግሞ የወደፊቷ ኢትዮጵያ ማሳያ ስለመሆናቸው ነው አማካሪው የተናገሩት፡፡ 

በተለይም ባለፈ ታሪካችን ያጣናቸው ብሔራዊ ጥቅሞችን መልሶ ለማግኘት መስራት ብልህነት ነው ያሉት አቶ ዘመዴነህ፤ ትልቅ ለውጥ የሚፈጥሩ ዘርፎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት ያለውን ፋይዳ አስታውሰዋል፡፡ 

አያይዘውም በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው ኢኮኖሚውን የሚያቃኑ ብሎም ከፍተኛ ግብር ከፋይ ለሆኑ የኢትዮጵያ ተቋማት የተደረገው ማበረታቻ ይሁን የሚያሰኝ ነው በማለት ድርጊቱ መንግስት አስተማማኝ እድገትን ለማረጋገጥ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ 

ኢትዮጵያ ራዕይን ወደ ድል እየለወጠች ነው ያሉት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው፤ ይህም ከእርሷ አልፎ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለኢኮኖሚ ነፃነት እንዲታገሉ ያነቃቃ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በአፎምያ ክበበው

#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #megaprojects