የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ከዓለም ባንክ እና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ዓመታዊ ጉባኤ ጎን ለጎን ከሳዑዲ የልማት ፈንድ ዋና ኃላፊ ሱልጣን አብዱራህማን አል-ማርሻድ ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።
በኢትዮጵያ እና በሳዑዲ ዓረቢያ መካከል ጠንካራ እና እያደገ የመጣ የልማት አጋርነት መፈጠሩ በውይይቱ ላይ ተነሥቷል።
አቶ አሕመድ ሽዴ የሳዑዲ የልማት ፈንድ ኢትዮጵያ ለምታደርጋቸው የልማት ጥረቶች ለሚያደርገው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
ሁለቱ ሀገራት ቅድሚያ በሚሰጧቸው የጋራ ኢኮሚያዊ ጉዳዮች ላይም ትብብርን የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ፤ በተለይም አዲሱን የዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግዙፍ ፕሮጀክት ጨምሮ ኢትዮጵያ በኢነርጂ እና በመሠረተ ልማት ዘርፎች ትልቅ ኢንቨስትመንት እንደሚያስፈልጋት አበክረው አስታውቀዋል።
ሱልጣን አብዱልራህማን አል-ማርሻድ በበኩላቸው፣ የሳዑዲ የልማት ፈንድ ሁለቱ ሀገራት ቅድሚያ በሚሰጧቸው የጋራ ፕሮጀክቶች ላይ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ይህ ድጋፍ ከኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት አጀንዳዎች ጋር በሚጣጣም መልኩ የሚደረግ መሆኑንም ነው ያስታወቁት።
በዮናስ በድሉ
#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #SaudiArabia #SFD