ይህን ያስተዋወቁት ቢአኤካ ግሩፕ እና የቻይናው የከባድ መኪና አምራች ኩባንያ ሻክማን በጋራ በመሆን ነው።
በመድረኩ ተሽከርካሪዎቹ ለኢትዮጵያ ገበያ ከዛሬ ጀምሮ ክፍት የተደረጉ ሲሆን፤ የቻይና መንግሥት እና የሻንሺ ግዛት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የሻክማን ኩባንያ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ይህ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የኢነርጅ ሽግግርን የሚያመጣ ቁልፍ ጅማሮ ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ በቀጣይም በአማራጭ ኃይል እንዲሁም በታዳሽ ኃይል የሚንቀሳቀሱ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ በስፋት ይገባሉ ተብሏል።

በብሩክታዊት አስራት
#ebcdotstream #ethiopia #lngvehicles #electricvehicles #china