Search

የኢትዮጵያን አንድነት ለማጠናከር ወሳኝ የሆነው የጋራ ትርክት

ረቡዕ ጥቅምት 12, 2018 40

በአርባ ምንጭ ዩንቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና የጂኦፖለቲካ መምህር የሆኑት ሰኢድ አሕመድ (ዶ/ር) ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ኢትዮጵያን ለዘመናት ወደኋላ ሲጎትቱ የነበሩት "ነጣይ ትርክቶች" መሆናቸውን አንስተዋል።
ጠላቶቻችን ኢትዮጵያ አንድ አሰባሳቢ ትርክት ካላት ኃያል እንደምትሆን ስለሚያውቁ አንድነታችንን እንደማይፈልጉም አብራርተዋል።
የኢትዮጵያ እድገት እና ሰላም የማይፈልጉ ኃይሎች በገዢ ትርክት እንዳንኖር የተለያዩ ጥረቶችን እንደሚያደርጉም ጠቁመዋል።
በአንድነት ከቆምን እንደ ዓድዋ ያሉ ታላቅ ድሎችን ማስመዝገብ እንዲሁም ከሀገራችን አልፎ ለአፍሪካም ገዢ ትርክት መፍጠር እንችላለን ብለዋል።
እነዚህን ነጣይ ትርክቶች በመጣል የጋራ ትርክት በመገንባት ኃያል ሀገርን መገንባት እንደሚቻልም ሰኢድ አሕመድ (ዶ/ር) አመላክተዋል።
ጠንካራ የጋራ ትርክት ለመገንባት ሁሉም ዜጋ ሀገሩን እንዲያስብ ማድረግ፣ ልዩነቶች ቢኖሩም በሀገራዊ ጥቅም የማይደራደር ዜጋ መፍጠር እንዲሁም ቱባ ባህልና እሴቶቻችንን ከዘመናዊነት ጋር ማጣመር እንደሚያስፈልግም አብራርተዋል።
 
በሜሮን ንብረት