Search

ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ ማድረግን ያለመው የዘመናዊነት እሳቤ

ረቡዕ ጥቅምት 12, 2018 58

በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ዘመናዊ የመልሶ ማልማት ሥራዎች ተከናውነዋል።
የከተሞች መዘመን ፋይዳው ዘርፈ ብዙ መሆኑን ያነሱት በከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ የፖሊሲ አማካሪ ያሬድ ተሾመ ናቸው።
ከተሞች የማዘመን ሂደት ቤቶችን እና ሕዝብ ተኮር ምቹ መንደሮችን መገንባት፣ ፈጣንና ቅልጥፍና ያለው አገልግሎት መስጠት እንዲሁም አረንጓዴና ጤናማ ከባቢ ያለው ከተማ መፍጠርን ያጠቃልላል ይላሉ።
በተጨማሪም ዘመናዊ ከተሞች ማኅበራዊነትን የሚያጠናክሩና ብዝሃ-ብሔራዊነትን የሚያንጸባርቁ መሆን እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
በዚህ ረገድ በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እየታዩ መሆኑን አንስተዋል።
በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ተስፋዬ ዘውዴ በበኩላቸው፣ ዘመናዊ ከተሞች ኢንቨስተሮችንና ቱሪስቶችን መሳብ እንዳለባቸው ገልጸው፣ ለዚህም በሰው ሰራሽ አስተውሎት መሳሪያዎች ታግዞ በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
 
በሴራን ታደሰ