Search

ባህርዳር በጣና ፎረም የሚሳተፉ እንግዶቿን እየተቀበለች ነው

ሓሙስ ጥቅምት 13, 2018 37

11ኛው የጣና ፎረም ከነገ ጀምሮ ለሦስት ቀናት በባህርዳር እና በአዲስ አበባ ከተሞች ይካሄዳል።
በባህርዳር ከተማ በሚካሄደው ፎረም የሚሳተፉ የተለያዩ ሀገራት እንግዶች ወደ ባህርዳር ከተማ እየገቡ ነው።
ተሳታፊ እንግዶች ባህርዳር በላይ ዘለቀ አየር ማረፊያ ሲደርሱም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገዋል።
 
ፎረሙ "አፍሪካ በተለዋዋጩ የዓለም ሥርዓት" በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄድ ሲሆን፤ በፎረሙ ላይ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እና ባለድርሻ አካላት በአህጉሪቷ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
11ኛው ጣና ፎረም ከጥቅምት 14 እስከ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በባሕዳር እና በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን የሀገራት መሪዎች፣ የተቋማት የሥራ ኃላፊዎች እና በርካታ የመገናኛ ብዙኀን ሙያተኞች የሚታደሙበት ነው።
 
በሳሙኤል ወርቃየሁ