Search

ቅዳሜ እና እሁድ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ንቅናቄ

ዓርብ ጥቅምት 14, 2018 31

በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ በሀገር አቀፍ ደረጃ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ንቅናቄ እንደሚካሄድ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታወቀ።

በዚሁ መሠረት በክልል ደረጃ የሚገኙትን ጨምሮ ሁሉም የምዝገባ ጣቢያዎች ቅዳሜ እና እሁድ ሙሉ ቀን ለምዝገባ ክፍት እንደሚሆኑ በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽህፈት ቤት የባለድርሻ አካላት እና የህዝብ ግኑኝነት ዳይሬክተር ሳሚናስ ሰይፉ ገልጸዋል።

እስከአሁን ድረስ 26.6 ሚሊዮን ዜጎችን መመዝገብ መቻሉን ጠቅሰው፤ በንቅናቄው አጠቃላይ የተመዝጋቢውን ቁጥር ወደ 27 ሚሊዮን ለማድረስ መታቀዱንም ዳይሬክተሩ ለኢቲቪ ተናግረዋል።

ንቅናቄው ያስፈለገው በዋናነት በየሳምንቱ ከሰኞ እስከ አርብ በሥራ ላይ የሚቆዩ ዜጎችን በሳምንታዊ የረፍት ጊዜያቸው እንዲመዘገቡ ለማስቻል ነው ብለዋል። 

በዘንድሮው ዓመት የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችም የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ መያዝ እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመው፤ ፋይዳ የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ ረገድ የራሱን ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም አክለዋል።

በሀብተሚካኤል ክፍሉ