Search

በጀግኖቿ መስዋዕትነት ሉዓላዊነቷ እንደተከበረ ከዘመን ዘመን የተሸጋገረች ሀገር - ኢትዮጵያ

ቅዳሜ ጥቅምት 15, 2018 52

“የማትደፈር ሀገር የማይበገር ሠራዊት” በሚል መሪ ሃሳብ 118ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን ቢሾፍቱ በሚገኘው የባህር ኃይል የስልጠና ማዕከል እየተከበረ ይገኛል።
በክብረ በዓሉ ላይ፣ ኢትዮጵያ በርካታ ውስብስብ ችግሮችን አልፋ በጀግኖች አርበኞች መስዋዕትነት ከትውልድ ወደ ትውልድ ነጻነቷና ሉዓላዊነቷ እንደተከበረ የተሸጋገረች ሀገር ናት ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለፁ።
በክብረ በዓሉ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች፣ አባት አርበኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የውጭ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች እና እንግዶች ተገኝተዋል።
 
በምንተስኖት ይልማ