ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተመዘገቡ ስኬቶች ሳንዘናጋ ቀሪ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ ይሰራል ሲሉ ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከካቢኔ አባላት ጋር የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸምን በተመለከተ በኮይሻ ግድብ ውይይት አድርገዋል።
ሰሞኑን ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ፣ ያሉትንም አጠናክሮ መቀጠል ልዩ ትኩረት የተሰጠው ሥራ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሕዳሴ ግድብ ከተመረቀ በኋላ የወልመል መሥኖ ፕሮጀክት መከተሉንም ጠቁመዋል።
በእነዚህ ድሎች ላለመዘናጋት የኮይሻ ግድብ የሥራ ሂደት በዝርዝር መታየቱን ገልጸው፣ “ከዚህ ቀደም ከምናውቀው ያለበት ደረጃ፣ ወደ ፊት በምን ያህል ጊዜ ፣ ምን ልናሳካ እንችላለን የሚለው ላይ በቂ የሆነ መረጃ አግኝተናል” ብለዋል።
በወቅቱ በዋና ዋና ጉዳዮች፣ በማክሮ ኢኮኖሚ እና በየዘርፉ በዝርዝር መረጃዎች ታግዞ የ100 ቀናት የመንግስት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተደርጓል።
በዮናስ በድሉ