Search

የኮሪደር ልማት ከግንባታ ባሻገር ሰብዓዊ ልማትን ያገናዘበ የዘመናዊ ከተማ ማሳያ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

ቅዳሜ ጥቅምት 15, 2018 45

በዘመናዊ መልክ የተገነባው የሳር ቤት-ጀርመን አደባባይ-ጋርመንት እና ፉሪ አካባቢ የኮሪደር ልማት ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
የኮሪደር ልማቱ እጅግ ማራኪ እና ምቹ ሆኖ መገንባቱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናግረዋል።
 
ከዚህ ቀደም አካባቢው ለትራፊክ ፍሰትም ሆነ ለነዋሪዎች ምቹ እንዳልነበረ አስታውሰው፤ አሁን ግን በኮሪደር ልማቱ ውብ መንገዶችን እና ዘመናዊ መዝናኛ ስፍራዎች መገንባታቸውን ገልፀዋል።
የኮሪደር ልማቱ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ያካተተ መሆኑንም አክለዋል። ይህ ደግሞ ታዳጊዎችን በስፖርት ዘርፍ ለማብቃት ትልቅ ሚና እንደሚኖረው አስረድተዋል።
የእግረኛ መንገዶቹም ለእግር ጉዞ እና ለብስክሌት ስፖርት ምቹ ሆነው መዘጋጀታቸውን ጠቅሰዋል።
በአካባቢው ልማት በርካታ የሥራ ዕድሎች መፈጠራቸውንም አመልክተዋል። የኮሪደር ልማት ለከተማ ልማት ወሳኝ አስተዋፅኦ ያለው መሆኑንም አብራርተዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የኮሪደር ልማት በከተሞች ብቻ ሳይሆን በገጠር አካባቢዎችም መጀመሩን አስታውቀዋል።
በአካባቢው የተተከሉት በርካታ ዛፎችም በቀጣይ ዓመታት ወደ ትልቅ ደንነት የማደግ ዕድል እንዳላቸው አመላክተዋል።
 
በሜሮን ንብረት