Search

“እንደ እኔ የተሰቃዩትን ከስቃያቸው መፈወስ ትልቅ ደስታ ይሰጠኛል”፦ በሐምሊን ፊስቱላ ማዕከል ከታካሚነት እስከ አገልጋይነት የዘለቁት እናት

እሑድ ጥቅምት 16, 2018 36

በዶ/ር ካትሪን እና በዶ/ር ሬጂናልድ ሐምሊን ከተመሠረተ ከ65 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው ሐምሊን የፊስቱላ ማዕከል ችግሩ ላጋጠማቸው በርካታ ሴቶች የሕክምና ድጋፍ ሲያደርግ የቆየ ተቋም ነው።

ማዕከሉ ከሚሰጠው የፊስቱላ ሕክምና አገልግሎት ባሻገር ታካሚዎቹን በተለያዩ ሙያዎች በማሰልጠን በዚያው በተቋሙ ውስጥ እንዲያገለግሉም ዕድል ይሰጣል።

በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ሐምሊን ፊስቱላ ማዕከል በጎ ፈቃደኛ እና ረዳት አገልጋይ የሆኑት ማሚቱ ጋሼ፤ በወሊድ ምክንያት ችግር ደርሶባቸው ነበር ከበርካታ ዓመታት በፊት ወደ ሆስፒታሉ የመጡት።

በሐምሊን የፊስቱላ ማዕከል ታክመው ከሕመማቸው ካገገሙ በኋላም በዚያው በማዕከሉ የሕክምና ስልጠና ወስደው በርካታ ሴቶችን እያገለገሉ የሚገኙ እናት ናቸው።

ዶ/ር ሬጂናልድ ቀዶ ሕክምና ሲሠሩ ከስር ስር እየተከተሉ ሥራቸውን እንዲመለከቱ በማድረግ እንዳስተማሯቸው ይገልጻሉ።

ዶ/ር ሬጂናልድን፣ አባዬ፤ ካትሪንን ደግሞ እማዬ እያሉ የሚጠሩት ማሚቱ ጋሼ፤ ሥራዬን በጣም ነው የምወደው፣ እንደ እኔ የተሰቃዩትን ከስቃያቸው መፈወስ ትልቅ ደስታ ይሰጠኛል ይላሉ።

ሕምተኞችን ማገልገል በእጅጉ እንደሚያስደስታቸው የሚገልጹት በጎ ፈቃደኛ አገልጋይዋ፤ የተማሩትን እና በልምድ ያገኙትን ዕውቀት ለሌሎች ከማጋራት ባሻገር ‘ሂሊንግ ላይቭስ’ የተሰኘ በእርሳቸው የሕይወት ተሞክሮ ላይ የተመሠረተ መጽሐፍ ስለመታተሙም ገልጸዋል።

በቢታንያ ሲሳይ

#ebcdotsteram #hamlin #fistulahospital #addisababa