Search

ከ63 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የጤና መድህን ተጠቃሚ ሆነዋል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ማክሰኞ ጥቅምት 18, 2018 69

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ እንደተናገሩት፣ በሀገሪቱ ከ63 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የጤና መድህን ተጠቃሚ ሆነዋል።
በጤናው ዘርፍ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የመድኃኒት አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ በሀገር ውስጥ የማምረት ሥራ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል። በመድኃኒት ላይ 60 ቢሊዮን ብር ድጎማ መደረጉንም አያይዘው ገልጸዋል።
የካንሰር ሕክምና ወጪ 60 በመቶ የሚሸፈነው በመንግሥት መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በጤናው ዘርፍ የውጭ ኢንቨስትመንቶች እንዲመጡ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም አንስተዋል።
ለጤናው ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ከ1 ሺህ በላይ አልጋ ያለው ማዕከል መገንባቱንም አስታውሰዋል።
እየተሰሩ ያሉት ሥራዎች ጅምር በመሆናቸው ብዙ ሥራዎች እንደሚጠበቁብንም አመላክተዋል።
 
በሜሮን ንብረት