Search

በአማራ ክልል ያለውን አንፃራዊ ሰላም ለማፅናት የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል

ረቡዕ ጥቅምት 19, 2018 74

በአማራ ክልል የታየውን አንፃራዊ ሰላም ለማፅናት የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተጠየቀ።
በባህር ዳር ከተማ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች በወቅታዊ የሰላም ጉዳይ ላይ እየተወያዩ ነው።
ባህር ዳር ከተማ ሰላሟን አስጠብቃ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እያከናወነች ነው ያሉት የከተማ አስተዳደሩ የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ ጌትነት አናጋው፤ ይህን ሰላም ለማፅናት በጋራ መሥራት ይጠይቃል ብለዋል።
የከተማዋን ብሎም የክልሉን አንፃራዊ ሰላም ለማፅናትም የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው፤ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ጠይቀዋል።
በውይይት መድረኩ ከከተማዋ የተውጣጡ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች እየተሳተፉ ነው።
በሳሙኤል ወርቃየሁ