Search

ከእስራኤል የመጣ የሐኪሞች ቡድን ነፃ የዓይን ሕክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው

ሓሙስ ጥቅምት 20, 2018 44

የእስራኤል የሐኪሞች ቡድን በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ነፃ የዓይንክምና አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ዛሬን ጨምሮ ለ4 ቀናት የሚቆየው የሕክምና አገልግሎቱ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለመጡ የዓይንክምና ፈላጊዎች የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ ዘርፎች በትብብር ትሠራለች ያሉት በኢትዮጵያ እናአፍሪካ ህብረት የእስራኤል ምክትል አምባሳደር ቶሜር ባር ላቪ፤ የአሁኑ የሕክምና አገልግሎትም የትብብሩ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ እና እስራኤል በግብርና፣ በቴክኖሎጂ እና በጤና ዘርፎች ያላቸውን ትብብር አስፍተው ለመቀጠል እንደሚሠሩም አምባሳደሩ ገልጸዋል።

የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍስሃ ጌታቸው (/)፥ በሕክምናው 40 የሚደርሱ የተለያዩ የዓይን ጤና ችግር ያለባቸው ህፃናት እና ሌሎች አዋቂዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል።

የእውቀት ሽግግር በማድረግ በቀጣይ ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች ተመሳሳይ የዓይን ሕክምናዎችን በራስ አቅም ለማከናወን እንዲችሉ እንደሚሠራም ተናግረዋል።

ሕክምናውን የእስራኤሉማሻቭ” ዓለም አቀፍ የልማት ተቋም የሚሰጠው ሲሆን፤ ከነፃ ሕክምናው በተጨማሪ 25 ሺህ ዶላር የሚያወጣ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።

በአስረሳው ወገሼ

#ebcdotstream #ethiopia #israel #freemedicalservice