የተሻሻለው የጤና ፖሊሲ በዘርፉ ያሉ የፋይናንስ ብሎም የአቅም ግንባታ ውስንነት ችግሮችን የሚፈታ ነው ሲሉ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ገለጹ።
የቀድሞው የጤና ፖሊሲ “በሽታን መከላከል” ላይ ይበልጡን ያተኮረ እንደነበር ያነሱት ዶ/ር መቅደስ፤ የተሻሻለው ፖሊሲ ግን “አክሞ ማዳን” ላይ ያተኮረ መሆኑን ተናግረዋል።
የፖሊሲው መሻሻል የጤና ተቋማት መስፋፋት፣ የግብዓት መሟላት እና የጤና መድህን ተደራሽነትን ጨምሮ በርካታ ጥቅሞችን ማስገኘቱን ሚኒስትሯ አብራርተዋል።
አያይዘውም፥ ከ60 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የጤና መድህን ተጠቃሚ ስለመሆናቸው ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም አዲሱ የጤና ፖሊሲ የግሉ ዘርፍ ከመንግሥት ጋር ያለው ትብብር አንድ ርምጃ እንዲራመድ ማስቻሉን ዶ/ር መቅደስ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።
በአዲሱ ፖሊሲ መድኃኒት በሀገር ውስጥ የማምረት አቅምን በማጎልበት ለግዢ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ ለማዳን ትኩረት ስለመሰጠቱም አክለው ገልጸዋል።
በአፎሚያ ክበበው
#ebcdotstream #ethiopia #ministryofhealth #newhealthpolicy