Search

ዝክረ ሰሜን ዕዝ በማዕከላዊ ዕዝ

ሰኞ ጥቅምት 24, 2018 99

በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈፀመው ጥቃት አምስተኛ ዓመት መታሰቢያ ክብረ በዓል "እንዳይደገም፤ መቼም አንረሳውም" በሚል መሪ ሃሳብ በማዕከላዊ ዕዝ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች እየተከበረ ይገኛል።
የመከላከያ ሠራዊት አባላት ክስተቱ እንዳይደገም የምናስብበት እና የተሠዉትን ሰማዕታትን የምናስታውስበት ቀን ነው ብለዋል።
ክስተቱ መቼም ሊደገም የማይገባው መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል፡፡
በጀግንነት ሃገርን መጠበቅ በቅንነት ሕዝብን ማገልገል መለያው የሆነው መከላከያ ሠራዊት በሰንደቅ ዓላማ ስር የገባውን ቃል ኪዳን ለመጠበቅ እየሠራ መሆኑ ተመላክቷል።
መከላከያ የሀገር ሉዓላዊነት ከማስከበር እና ሰላምን ከማስፈን ባለፈ የማኅበራዊ አገልግሎቶች ላይ በስፋት እየተሳተፈ መሆኑም ተገልጿል።
በመድረኩ የመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ፣ የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ እና ጥሪ የተደረገላቸው የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
 
በራሄል አብደላ