Search

"ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ ሰላም እና መረጋጋት ያላት አስፈላጊነት ይበልጥ እያደገ መጥቷል" - ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን

ማክሰኞ የካቲት 10, 2018 46

የቱርክዬ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መስኮች ላስመዘገቡት ስኬት “እንኳን ደስ አለዎት” በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንት ኤርዶዋን ይህን ያሉት ዛሬ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር በመሆን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የሚገኙት ፕሬዚዳንቱ፥ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የትብብር ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ በርካታ ስምምነቶችን ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ስምምነቶቹ ባቡርን ጨምሮ የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ማስፋፋት፣ የፋብሪካዎች ግንባታ፣ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ዝርጋታ እና የቱሪዝም ልማትን እንደሚያካትቱ አብራርተዋል።

ፕሬዚዳንት ኤርዶዋን ረጅም የሀገረ መንግሥት ታሪክ እና የተረጋጋ አስተዳደር ያላት ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ ሰላም እና መረጋጋት አስፈላጊነቷ ይበልጥ እያደገ መጥቷል ብለዋል።

ቱርክዬ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ምዕተ ዓመታትን ያስቆጠረ ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ ከፍተኛ ትኩረት እንደምትሰጥም አክለዋል።

በላሉ ኢታላ

#Ethiopia #Turkiye #Diplomacy #AbiyAhmedAli #RecepTayyipErdoğan #EthiopianBroadcastingCorporation #EBC #EBCdotstream