Search

ኢትዮጵያ እና ቱርክዬ በጋራ ለመፈፀም የተግባቡባቸው የስምምነት አጀንዳዎች እና ነጥቦች

ማክሰኞ የካቲት 10, 2018 744

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን ጋር በብሔራዊ ቤተመንግሥት በሰጡት የጋራ መግለጫ ሁለቱ ሀገራት በጋራ ለመፈፀም የተግባቡባቸውን የስምምነት አጀንዳዎች እና ነጥቦች ዘርዝረዋል።

 

I. የንግድ እና ኢኮኖሚ ትብብር 

✅ የንግድ ልውውጥ መጠን፦ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ ቢያንስ ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እና ከዚያም በላይ ለማሳደግ ታቅዷል።

✅ የዘርፍ ብዝሃነት (Diversification)፦ የንግድ ግንኙነቱ በተወሰኑ ምርቶች ላይ ብቻ ሳይወሰን የተለያዩ የቢዝነስ ዘርፎችን እንዲያካትት ስምምነት ላይ ተደርሷል።

✅ የቱርክዬ ኢንቨስትመንት፦ ታዋቂ የቱርክዬ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት በማድረግ ለሀገር ውስጥ እና ለጠቅላላው የአፍሪካ ገበያ የሚሆኑ ምርቶችን እንዲያመርቱ እና ኤክስፖርት እንዲያደርጉ ድጋፍ ለማድረግ ተስማምተዋል።

 

II. የባህር በር እና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ 

✅ ኢትዮጵያ ያቀደችውን የ10.2 በመቶ ዕቅድ ለማሳካት የባህር በር ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።

✅ ለኢትዮጵያ ዕድገት ማነቆ (bottleneck) የሆነውን የሎጂስቲክስ ችግር ለመፍታት የባህር በር ቁልፍ መሆኑ ታምኖበታል።

✅ ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባሕር በር እንድታገኝ ቱርክዬ በዲፕሎማሲው መስኩ የራሷን ጫና በመፍጠር የበኩሏን ሚና እንድትጫወት ከስምምነት ተደርሷል።

 

III. የፀረ-ሽብር ትግል እና አካባቢያዊ ጉዳዮች 

✅ ኢትዮጵያ እና ቱርክዬ በፀረ-ሽብር ትግሉ ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል።

✅ የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ ቱርክዬ ዘንድሮ የምታዘጋጀውን የኮፕ (COP) ስብሰባ በሚቀጥለው ዓመት ለኢትዮጵያ የምታስረክብ በመሆኑ፣ በዝግጅት ሂደት ውስጥ የልምድ ልውውጥ እና መደጋገፍ ለማድረግ ተስማምተዋል።

 

IV. ሥልታዊ እና ቀጣናዊ ግንኙነት 

✅ አፍሪካ በቀጣይ 20 እና 30 ዓመታት ውስጥ የሚኖራትን ከፍተኛ የኢኮኖሚ ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ቱርክዬ በአፍሪካ ዕድገት ውስጥ ያላትን የጂኦግራፊያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሚና እንድትወጣ መግባባት ላይ ተደርሷል።

✅ በኢትዮጵያ እና በቱርክዬ መካከል ያለውን ጥንታዊ ግንኙነት በመከባበር እና በመደጋገፍ ላይ ተመሥርቶ ይበልጥ ለማጠናከር መሪዎቹ ቃል ገብተዋል።

 

#Ethiopia #Turkiye #Diplomacy #AbiyAhmedAli #RecepTayyipErdoğan #EthiopianBroadcastingCorporation #EBC #EBCdotstream

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: