130 ሚሊዮን ሕዝብ የባሕር በር አጥቶ መኖር ፍትሐዊ አለመሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ከሚገኙት የቱርክዬ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን ጋር በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።
ኢትዮጵያ በጠላቶቿ ደባ የባሕር በር ተዘግቶባት መቆየቷን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሀገሪቱ የመልክዓ ምድር እስረኛ ሆና መቆየቷ ፈጽሞ ትክክል እንዳልሆነም አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።

እንደ ቱርክዬ ያሉ ወዳጅ ሀገራት አስፈላጊውን የዲፕሎማሲ ጫና በመፍጠር፣ ኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄዋን በሰላማዊ መንገድ እንድታሳካ ድጋፍ እንዲያደርጉ ከፕሬዚዳንት ኤርዶዋን ጋር በጥልቀት መወያየታቸውን ጠቅሰዋል።
ሎጂስቲክስ እና የባሕር በር ለኢትዮጵያ ዕድገትና ብልጽግና ወሳኝ መሆናቸውን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ፕሬዚዳንት ኤርዶዋን በዚህ ረገድ ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ከመግባባት ላይ መድረሳቸውን ገልጸው፤ ለተደረገው ውጤታማ ውይይትም ምስጋና አቅርበዋል።
በለሚ ታደሰ
#Ethiopia #SeaAccess #EthiopiaTurkiye #AbiyAhmed #Erdogan #Diplomacy