Search

በሰሜን ዕዝ ላይ የደረሰው ድርጊት እንዳይደገም ሲዘከር ይኖራል - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

ሰኞ ጥቅምት 24, 2018 65

የሰሜን ዕዝ ጥቃት የተፈፀመበት 5ኛ ዓመት፣ ዝክረ ሰሜን ዕዝ “እንዳይደገም መቼም አንረሳውም!” በሚል መሪ ሐሳብ በቢሾፍቱ አየር ወለድ ግቢ ታስቧል።
የኢፌዴሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ መከላከያ ሠራዊቱ መሥዋዕትነት እየከፈለ ሀገር ሲጠብቅ መኖሩን በማንሣት፣ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ ላይ የደረሰው ጥቃት ሊደገም የማይግባው ድርጊት ነው ብለዋል።
ሰሜን ዕዝ ከ20 ዓመታት በላይ ዳር ድንበር በመጠበቅ እና በልማት ባለውለታ የነበረ ሠራዊት እንደነበርም አስታውሰው፣ በተቃራኒው በዕዙ ላይ የተፈፀመው ድርጊት እንዳይደገምም መዘከር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ ቀን ሲታሰብም ለሀገር ሉዓላዊነት ሲሉ የተሠዉ ጀግኖችን ለመዘከር፣ የተፈፀመውን ድርጊት በማውገዝ ትውልድ እንዲማርበት እና ለተዋደቁት ተገቢውን ክብር ለመስጠት መሆኑን በመከላከያ ሠራዊት የሥነ-ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን ተናግረዋል።
በሙሉ ግርማይ