የፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ. ዴሌቦ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በነገው ዕለት በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን እንደሚፈፀም የቀብር አስፈፃሚ ኮሚቴ አስታወቀ።
በነገው ዕለት ከረፋዱ 5 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር አሸኛኘት እንደሚደረግላቸው የቀብር አስፈፃሚ ኮሚቴው ገልጿል።
የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ደግሞ ከቀኑ 7 ሰዓት ሰዓት በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን አንደሚፈፀም ተገልጿል።
ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ. ዴሌቦ ባጋጠማቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በትናንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።