Search

የጅማ ዩኒቨርሲቲ የቃልኪዳን ቤተሰብ ምስረታ

ሓሙስ ኅዳር 04, 2018 98

ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር የሚያስችል" የጅማ የቃል ኪዳን ቤተሰብ (ሀመና)" የተሰኘ የስምምነት ማስጀመርያ መረሐ ግብር በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተከናወኗል።

ስምምነቱ በጅማ ከተማ ማኅበረሰብ እና በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል ጥብቅ ቤተሰባዊ ትስስር በመመስረት በወዳጅነት እና ኢትዮጲያዊ አንድነትን በማጠናከር ምቹ የትምህርት ጊዜ፣ የመማር ማስተማርና የምርምር አከባቢ ለመፍጠር የሚያስችል ነው።

"ሀመና" የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ስምምነት የጅማ ዩኒቨርሰቲ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ተግባራዊ ያደረገው ነው።

በየዓመቱ ወደ ጅማ ዩኒቨርሰቲ የሚመጡ ተማሪዎች ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመተባበር፤ በጅማ ከተማ የሚኖሩ ፈቃደኛ ኗሪዎች ለአዳዲስ ተማሪዎች ቤተሰባዊ ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ ጥሩ የትምህርት ጊዜ እንዲኖራቸው ያስችላልም ተብሏል።

2012 . በጎንደር ዩኒቨርሰቲ ተግባራዊ መደረግ የጀመረው "የቃል ኪዳን ቤተሰብ" አዳዲስ ተማሪዎችን ያለምንም ስጋት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ታስቦ ተማሪዎች ከማኅበረሰብ ጋር ቤተሰባዊ ግንኙነት እንዲኖራቸው ያስቻለ አራያነት ያለው ፕሮጀክት ሆኗል።

በራሄል አብደላ