Search

ሠላምን ለማጽናት እሴቱን ማጎልበት ያስፈልጋል - ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ሓሙስ ኅዳር 04, 2018 98

ሠላምን ለማጽናት እሴቱን ማጎልበት እንደሚያስፈልግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ተናገሩ።
አቶ ጥላሁን ይህን የተናገሩት በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ባለው 5ኛው ሀገር አቀፍ የሠላም ጉባዔ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ነው።
ሠላም የሚመጣው በመለያየት ሳይሆን በጋራ ተፈቃቅዶ መኖር ሲቻል መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት ተናግረዋል።
በሠላም እሴት ግንባታ እስከአሁን ከተሠራው ሥራ ይልቅ ወደፊት የሚጠብቀን የቤት ሥራ ይበልጣል ያሉት አቶ ጥላሁን፤ የሃይማኖት ተቋማት ትውልድን የማነጽ ሥራን በአስተምህሮአቸው አካትተው ማከናወን ይጠበቅባቸዋል ሲሉም አመላክተዋል።
የጉባዔው የ2ኛ ቀን ውሎ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አባያ ካምፓስ ስታዲየም እየተካሄደ ያለ ሲሆን፤ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂዎች፣ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የፀጥታ ተቋማት ተወካዮች እና የአባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በተመስገን ተስፋዬ