Search

ኢትዮጵያን በሚመጥን መልኩ የሚከበረው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን

ሓሙስ ኅዳር 04, 2018 182

20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን "ዴሞክራሲያዊ መግባባት፣ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሆሳዕና ከተማ ይከበራል።
በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር የተመራ ልዑክ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችንና የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን ተመልክቷል።
 
በዓሉ የሚከበርበት የአቢዮ ኤርሳሞ ሁለገብ ስታዲየም ጥገናና ተጨማሪ ሥራዎች እንዲሁም የክልሉ ተቋማት የሕንፃ ግንባታ የሥራ እንቅስቃሴዎችም ከተጎበኙ ሥራዎች መካከል ናቸው።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ፤ በዓሉን በድምቀት ለማክበር በርካታ ዝግጅቶች መደረጋቸውን አስታውቀዋል።
ክብረ በዓሉ ኢትዮጵያን በሚመጥን መልኩ ይከበራል ሲሉም ተናግረዋል።
የዘንድሮው ክብረ በዓል የጋራ ትርክት ውጤት የሆነውን ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ባስመረቅንበት ማግስት እንዲሁም የተለያዩ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች በተጀመሩበት ማግስት የሚከበር መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ሕዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም ይከበራል።
 
በሀይማኖት ከበደ