የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ እና የ2018 በጀት ዓመት የበጋ ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሂዷል።
በመድረኩም በክረምት ወራት የተከናወነው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳትፎ በበጋ ወራትም ተጠናክሮ እንዲቀጥል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር ጥሪ አቅርበዋል።
የክልሉ ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ በበኩላቸው፤ በክልሉ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ364 ሺ በላይ ሰዎችን በማሳተፍ ከ937 ሺ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደቻለ ተናግረዋል።
የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ፣ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ፣ የማዕድ ማጋራትን ጨምሮ በ14 የተለያዩ ዘርፎች የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራ ሲከናወን መቆየቱን ጠቅሰው፤ በበጋ ወቅትም የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶቹ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል።
በነስረዲን ሀሚድ