Search

ዩናይትድ ኪንግደም ኢትዮጵያ ኮፕ 32ትን ለማዘጋጀት በመመረጧ መደሰቷን አስታወቀች

ቅዳሜ ኅዳር 06, 2018 57

በብራዚል ቤሌም እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ከዩናይትድ ኪንግደም የአየር ንብረት ሚኒስትር ኬቲ ዋይት ጋር ተወያይተዋል።
ከጉባኤው ጎን ለጎን በተደረገው ውይይት የዩናይትድ ኪንግደም የአየር ንብረት ሚኒስትር፤ ኢትዮጵያ 32ኛውን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለማዘጋጀት በመመረጧ እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን የአየር ንብረት ለውጥ የችግሩ ገፈት ቀማሽ የሆኑ አፍሪካውያንን ድምፅ ከፍ አድርጎ በማሰማት ለተግባራዊ እርምጃ ሁሉም እንዲሰራ የምታስተባብርበት መድረክ መሆኑንም አንስተዋል።
ጉባኤው በስኬት እንዲስተናገድ በማድረጉ ሒደት ከኢትዮጵያ ጎን በትብብር እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል።
ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ሥራዎችን በስፋት አንስተዋል።
ኢትዮጵያ እያከናወነችው ያለው የአረንጓዴ እሳቤ እርምጃዎችን ዩናይትድ ኪንግደም እውቅና እንደምትሰጥ ገልፀው፤ ችግሩን ለመፍታት ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ የመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው አመላክተዋል።
 
በሀብታሙ ተክለስላሴ