Search

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከአዘርባጃን ቀዳማዊት እመቤት መህሪባን አሊዬቫ ጋር ተወያዩ

ዓርብ የካቲት 20, 2018 44

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ጋር በአዘርባጃን ባደረጉት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት፣ ከአዘርባጃን ቀዳማዊት እመቤት መህሪባን አሊዬቫ ጋር ውጤታማ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይታቸውም የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ቅድሚያ ሰጥቶ በሚሠራባቸው ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ በተለይም በሴቶች፣ በሕፃናትና በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ ባሉ ፕሮጀክቶች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሁለቱ ቀዳማዊት እመቤቶች በማኅበራዊ ልማት ዘርፍ በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን፣ መህሪባን አሊዬቫ ተዛማጅ ማዕከላትን በመገንባትና የክህሎት ሥልጠናዎችን በማመቻቸት ረገድ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በቆይታቸው በባኩ አቅራቢያ የሚገኘውን የጋላ አርኪኦሎጂና የባህል ሙዚየምን እንዲሁም የአካል ጉዳተኞች የእደ ጥበብ ማምረቻ ማዕከልን ጎብኝተዋል።

ይህ ጉብኝት በኢትዮጵያ በተጋላጭ ዜጎች ላይ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ይበልጥ ለማጠናከር የሚረዳ ጠቃሚ ልምድ የተገኘበት መሆኑን ቀዳማዊት እመቤቷ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት ጠቅሰዋል።

#EBC #Ethiopia #Azerbaijan #FirstLadyEthiopia #ZinashTayachew #SocialDevelopment