በወዳጅነት አደባባይ የጡት ካንሰር የሚያስከትለውን ጉዳት ለማስገንዘብ ያለመ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሐ ግብር ተካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) የጡት ካንሰር የሴቶችን ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥል ሕመም መሆኑን ተናግረዋል።
ችግሩን ለመቀነስም ግንዛቤ ማስጨበጫን ጨምሮ ቅንጅታዊ አሠራርን ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

የመርሐ ግብሩ ተሳታፊዎችም የጡት ካንሰር የሚያስከትለውን ማኅበራዊ ተፅዕኖ ለመቀነስ ሁሉም የድርሻውን ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ9 ሺህ በላይ ሴቶች በጡት ካንሰር ምክንያት ሕይወታቸውን እንደሚያጡ የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
በይድነቃቸው ሰማው