Search

የከተሞች ፎረም ከተሞች የውስጥ አቅማቸውን እንዲያጠናክሩ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያግዝ ነው - ‎ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ

እሑድ ኅዳር 07, 2018 137

የከተሞች ፎረም ከተሞች የውስጥ አቅማቸውን እንዲያጠናክሩ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያግዛቸው መሆኑን የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ገለጹ።
ሚኒስትሯ በሰመራ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው 10ኛው የከተሞች ፎረምን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል።
በመግለጫቸውም፥ የከተሞች ፎረም ከተሞች የውስጥ አቅማቸውን እንዲያጠናክሩ እንዲሁም ከሌሎች እህትማማቾች ከተሞች ጋር በተለያዩ ዘርፎች ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አስችሏል ሲሉ ተናግረዋል።
‎መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት በኮሪደር ልማት ሥራ ከተሞች ለህብረተሰቡ ምቹ ከመሆን በተጨማሪ የገቢ አማራጮችን እንዲያሰፉ፣ በኢንዱስትሪ እና በኢንቨስትመንት መስፋፋትም ከፍተኛ ለውጥ እንዲያመጡ ማስቻሉን ገልጸዋል።
‎የከተሞች አገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ እንዲዘምን እና እንዲቀላጠፍም የኮሪደር ልማቱ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ጠቅሰዋል።
‎በፎረሙ እንዲሳተፉ በዕቅድ ከተያዙ 150 ከተሞች 143 ያህሉ በፎረሙ የተካፈሉ ሲሆን፤ በተጨማሪም 7 ሺህ ኤግዚቢሽን አቅራቢዎች መሳተፋቸውን ወ/ሮ ጫልቱ ገልጸዋል።
‎በከተሞች እየተከናወኑ በሚገኙ ዘርፈ ብዙ ልማቶች ለዜጎች የሥራ ዕድል በማመቻቻት በኩልም ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል።
‎በፎረሙ የዛሬ ውሎ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች በመቀመር እና የውስጥ አቅምን በማጎልበት የከተማ እና መሠረተ ልማት ዘርፉን ይበልጥ ማሳደግ የሚያስችል የፓናል ውይይት በመካሄድ ላይ ነው።
በሁሴን መሐመድ