የአፋር ክልል መሶብ (ኮራ) የአንድ ማእከል አገልግሎት በዛሬው ዕለት በይፋ ስራ ጀምሯል።
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ አገልግሎቱን መርቀው ስራ አስጀምረዋል።
በመርኃ ግብሩ ላይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባን ጨምሮ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ፣ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ሀይሌ (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የመሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ ህብረተሰቡ የዲጂታል አማራጮችን በመጠቀም አገልግሎቶችን በቀላሉ በአንድ ቦታ የሚያገኝበት ማእከል ነው።
#Ebc #Ebcdotstream #Ethiopia #Afar #MesobCenter