Search

ኢንስቲትዩቱ በሰራቸው ውጤታማ ሥራዎች በርካታ ሚሊዮን ዶላሮችን ማዳን ችሏል፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሰኞ ኅዳር 08, 2018 147

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በሠራቸው ውጤታማ ስሥራዎች በርካታ ሚሊዮን ዶላሮችን ማዳን ችሏል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እንደ ሀገር ትኩረት ከተሰጠባቸው ዘርፎች ዋንኛው ነው ያሉ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በበርካታ ዘርፎች ውጤታማ ሥራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡
በዋናነት በግብርና ላይ ምርት እና ምርታማነትን የሚያረጋግጡ ሥራዎች መሰራታቸውን አንስተዋል፡፡
በአገልግሎት ዘርፉ ደግሞ ሕዝብ ቅሬታ የሚያነሳባቸውን ሁኔታዎች በመለየት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
ለዚህም ዋንኛ ማሳያ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከመቶ በላይ የሚሆኑ አገልግሎት ሰጪዎች በአንድ ማዕከል ሥር ሆነው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡
የዚህ ሲስተም የተዘረጋውም በሀገር ልጆች መሆኑን እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከሰራቸው ሥራዎች የሚካተት ነው ብለዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ በተለያዩ ዘርፎች እስካሁን በሰራቸው ውጤታማ ሥራዎች በርካታ ሚሊዮን ዶላሮችን መቻሉን ነው ያመላከቱት፡፡
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በዋናነት የያዘው አቋም፣ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን ለሁሉም ዜጋ እንዲዳረስ መሆኑን ገልጸው፤ የመረጃ አያያዝ ሥርዓቶችን በማበልጸግ ግዙፍ የሆነ እና ዘመናዊ የመረጃ ቋት መሥራት መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በሀብተሚካኤል ክፍሉ