ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢፌዴሪ ኤምባሲ እና በአሜሪካ የንግድ ምክር ቤት የአሜሪካ-አፍሪካ የቢዝነስ ማዕከል ትብብር የተዘጋጀ የኢንቨስትመንት ማስተዋወቂያ መድረክ ተካሂዷል።
በንግድ ምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት በተካሄደው በዚህ መድረክ ላይ በርካታ ታዋቂ የአሜሪካ ኩባንያዎች ኃላፊዎች እና የቢዝነስ ተወካዮች ተሳትፈዋል።
በመድረኩ ላይ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልእክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም በኢትዮጵያ ለግሉ ዘርፍ ኢንቨስትመንት ያሉትን ምቹ ሁኔታዎች እና ሰፊ ዕድሎች በዝርዝር አቅርበዋል።
የአሜሪካ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ አምባሳደር ብናልፍ ጥሪ ማቅረባቸውን በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።