በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኡመር ጌሌህ አቅርበዋል።
አምባሳደሩ በዚሁ ወቅት፥ በጅቡቲ በሚኖራቸው የሥራ ቆይታ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ስትራቴጂያዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ እንደሚሠሩ ተናግረዋል።
ቀጣናዊ ትስስርን ለማጎልበት የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እንዲሁም ሰላም እና መረጋጋት እንዲፀና ለማስቻል በትኩረት እንደሚሠሩ ገልጸዋል።

በተጨማሪም የሁለቱን ሀገራት ትብብር ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ እንዲሁም የጋራ እሴቶችን ለማጎልበት ያላቸውን ቁርጠኝነት መግለጻቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
#ebcdotstream #ethiopia #djibouti #diplomacy