ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የተገኙ ስኬቶችን በማስቀጠል እና ሰላምን በማፅናት ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ እየተሠራ ነው ሲሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ ገለጹ።
በክልሉ “ከጂኦ - ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና” በሚል መሪ ሐሳብ ለፖሊስ አባላት ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው።
ርዕሰ መስተዳድሯ በመርሐ ግብሩ ላይ፥ ዘመን ተሻጋሪ የጀግንነት ታሪክ ያላት ኢትዮጵያ ዕድገቷን በማይመኙ ታሪካዊ ጠላቶቿ ሴራ ሳትደናቀፍ በአስደማሚ የዕድገት ጎዳና ላይ እንደምትገኝ ተናግረዋል።

ሀገሪቱ በልማት እና በዲፕሎማሲ የተገኙ ድሎችን በማስቀጠል ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በመሥራት ላይ መሆኗን ገልጸው፤ በመፍጠርና መፍጠን እሳቤ በመሥራት እና ፈተናን ወደ ስኬት በመቀየር ረገድ የጸጥታ አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በክልሉ ሰላምን በማፅናት የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በየደረጃው ከሚገኙ የጸጥታ አካላት ትልቅ ኃላፊነት የሚጠበቅ መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሯ ገልጸዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኡጉላ ኡጁሉ በበኩላቸው፥ የኅብረተሰቡን ሰላም እና ደኅንነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በሚፍታህ አብዱልቃድር
#ebcdotstream #Gambella #peace