Search

መንግሥት ለአካታች ልማት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ

ማክሰኞ ኅዳር 09, 2018 113

መንግሥት ለሰው ተኮር አጀንዳዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ለአካታች ልማት እየሠራ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ።
በደሴ ከተማ የተመለከትናቸው የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርት ግብይት ማዕከል እንዲሁም የእንጀራ መጋገሪያ አዳራሽ ሥራዎች የሕዝባችንን የየዕለት ችግሮች ለመፍታት ለምናደርገው ጥረት ማሳያዎች ናቸው ብለዋል።
የግብይት ማዕከሉ ዋና ዓላማ አምራቾች እና ሸማቾችን በማገናኘት እና በመካከል ያለውን የተንዛዛ የግብይት ሰንሰለት በማሳጠር ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ገበያን ማረጋጋት ነው ሲሉ ገልፀዋል።
 
ማዕከሉ የግብርና፣ የኢንዱስትሪ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን እና የእንስሳት ተዋጽዖዎች ግብይት እንደሚካሄድባቸው ጠቁመዋል።
በተጨማሪ የደሴ ከተማ የቧንቧ ውኃ የእንጀራ መጋገሪያ አዳራሽ ግንባታ እንጀራ በመጋገር ዘላቂ የሥራ ዕድል በመፍጠርና ምርታማነትን በማስፋፋት የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥን ዓላማ ያደረገ ነው ብለዋል።
የብልፅግና ጉዟችን ሁሉንም ማኅበረሰብ ተጠቃሚ በማድረግ ማኅበራዊ ፍትህን ያረጋገጠ ዘላቂ ልማትን በማምጣት ራዕይ የሚመራ ነው ሲሉ ገልፀዋል።