Search

የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለሶስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

ማክሰኞ ኅዳር 09, 2018 341

የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም ለሶስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፤ የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም ለሶስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ወደ ምድረ ቀደምት ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ ብለዋል።

ጉብኝታቸውም በማሌዢያ እና ኢትዮጵያ መካከል እያደገ ያለውን ወዳጅነት እና ትብብር የሚያሳይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አመልክተዋል።

ይህም በሀገራችን የብልጽግና ጉዞ ውስጥ በጠቃሚ ጊዜ የተደረገ ጉብኝት ነው ያሉት።